
አገሯን 'በሙስና ያራቆተችው' የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ - bbc news አማርኛ
Play all audios:

አገሯን 'በሙስና ያራቆተችው' የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ 20 ጥር 2020 የአፍሪካ ባለጸጋዋ ሴት አገሯን በሙስና እንዴት እንዳራቆተቻት መረጃዎች እየወጡ ነው። የደቡብ አፍሪካዊቷ አገር አንጎላ ተበዝባዧ አገር ነች። በዝባዧ ደግሞ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ልጅ ወይዘሮ
ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ናት። የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ልጅ የሆነችው ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ በመሬት፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ ዘይት ዘርፍ በመሰማራት የመንግሥትን እጅ በመጠምዘዝ ከድሃ አንጎላዊያን ጉሮሮ እየነጠቀች ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳካበተች ይነገራል። በተለይ አባቷ በመንግሥት ሥልጣን ላይ በነበሩበት
ወቅት የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእርሷ ብቻ ተብለው የሚከፈቱና የሚዘጉ ነበሩ። ሰሞኑን ይፋ ሆነ የሚባለው ዶክሜንት በእነዚህ ሥራዎች እንዴት ለእርሷና ባሏ ሁኔታዎች ይመቻቹላቸው እንደነበሩና ለመንግሥት መክፈል የነበረባቸውን ገንዘብ እንዴት እንዳልከፈሉ ያሳያል። በእርግጥ ወይዘሮዋ ሁሉም የተቀናበረብኝ
የሐሰት ክስ እንጅ እውነትነት የለውም የሚል ማስተባባያ ሰጥታለች። ኑሮዋን በእንግሊዝ ያደረገችው ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ በአገሯ ከዘረጋችው የቢዝነስ መረብ የምትሰበስበውን ረብጣ ዶላር በመጠቀም በማዕከላዊ ለንደን ፈርጠም ያሉ የቢዝነስ ተቋማትን እንደገነባች ይነገርላታል። Skip ብዙ የተነበቡ and
continue reading ብዙ የተነበቡ * "ኢሰመኮ የተዛባ ሪፖርት ያወጣ ነበር" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሱ * ትራምፕ በሎስአንጀለስ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ወታደሮች አሰማሩ * በዓለም አቀፍ የፋሽን መድረክ ተመራጭ የሆኑ ሞዴሎች መገኛዋ አገር * ቡና መጠጣት ለጤና ጠቃሚ ነው
ጎጂ? በምን ያህል መጠን? End of ብዙ የተነበቡ * ከጋዳፊ በኋላ ሰላም በራቃት ሊቢያ የሌሎች ሃገራት ፍላጎት ምንድነው? አሁን በርካታ ሰነዶች የኢዛቤልን የሙስና ሂደቶች የሚያጋልጡ መረጃዎች ከየአቅጣጫው ብቅ ማለታቸውን ተከትሎና ከጥቂት ዓመታት በፊት ከሥልጣን የወረዱት አባቷ ልጃቸውን መከላከል
በማይችሉበት ደረጃ ላይ ሲሆን የአንጎላ መንግሥት ኢዛቤል አንጎላ ውስጥ አላት የተባለው ሃብት ሁሉ ታግዶ ምርመራ እንዲካሄድበት አድርጓል። አሁን ቢቢሲ ከ700 ሺህ በላይ ያፈተለኩ መረጃዎች ስለወይዘሮዋ የቢዝነስ እንቅስቃሴና የሙስና መረቧ ደርሶታል። እነዚህ መረጃዎች በ37 ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት
የተጠናቀሩ ናቸው። ከነዳጅ ጋር በተያያዘ አንድ የለንደን የነዳጅ አውጭ ኩባንያ በአገሯ እንዲሰራ በተጭበረበረ መንገድ ሲገባ ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ የትወናው አካል ነበረች። በኋላ አባቷ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ሲታገድ 58 ሚሊዮን ዶላር የከፈለችበት ደረሰኝ ተገኝቷል። ይህ ለምን
እንደተፈጸመና ድርሻዋስ ምን ነበር የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። የወይዘሮ ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ጉዳይ በዚህ አያበቃም። አንድ ዱባይ ከሚገኝ ኩባንያ ጋርም በተመሳሳይ ተመሳጥራ ሁለት የክፍያ ሰነዶች እንደተላኩላት ማግኘት ተችሏል። ይህ ሕጋዊነት ይጎድለዋል የተባለው የክፍያ ሰነድም ለምን ክፍያው
እንደሚፈጸም የሚያትተው ነገር የለም። በዚህ የሂሳብ መጠየቂያም በአንደኛው 472,196 ዩሮ ሁለተኛው ደግሞ 928,517 የአሜሪካን ዶላር ተጠይቆበታል። ይህም ሰነድ ህጋዊነቱ ያልተረጋገጠ ቢሆንም ወይዘሮዋ ግን ሕጋዊ መንገድን ተከትየ የፈጸምኩት ነው ብላለች። ሌላኛው ከነዳጅና ኃይል አቅርቦት ጋር
በተያያዘ ለኢዛቤል የቀረበው ክስ በ2006 የአንጎላ የኃይል አቅርቦት ለመሥራት ስትስማማ በወቅቱ 15% ብቻ ከፍላ ቀሪው ዝቅተኛ ወለድ ተደርጎላት በተራዘመ ጊዜ እንድትከፍል ነበር። ላለፉት 11 ዓመታት ግን መክፈል የነበረባትን 70 ሚሊዮን ዶላር አልከፈለችም። አሁን ኢዛቤል በባለድርሻነት የምትመራው
ኩባንያ አጠቃላይ ዋጋው 750 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። * ሃሪና ሜጋን ያለባቸውን ዕዳ ሠርተው ሊከፍሉ ነው ተቋሟ እዳውን በ2017 ለመክፈል ተስማምቶ ነበር፤ ነገር ግን ቢያንስ ወለድ ተብሎ የታሰበውን 9% ማካተት ስላልቻለ ክፍያው እንዳይፈጸም ተደርጓል። ከአልማዝ ጋር በተያያዘ በሙስና ሥራው ኢዛቤል
ብቻዋን አትሳተፍም። ባሏም አጋሯ ነው። በ2012 ባለቤቷ ሲንዲካ ዶኮሎ መንግሥት ከሚቆጣጠረው ሶዳየም ከሚባለው የአልማዝ ኩባንያ ጋር የአንድ ወገን ፊርማ ፈርሟል። በፊርማው መሰረት ሁለቱ ፈራሚዎች የፕሮጀክቱን ወጪ ግማሽ ግማሽ መቻል ነበረባቸው። ነገር ግን ሙሉ ወጭው የተሸፈነው በመንግሥት ነው።
ሰሞኑን የሚዲያዎች እጅ ላይ የገባው ዶክመንት እንደሚያሳየው ከ18 ወራት በኋላ ዶኮሎ 79 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ሲገባው የከፈለው የገንዘብ መጠን ግን 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ ጉዳዩን ስለደለልኩ ሽልማት ይገባኛል ብሎ ከዚሁ ፕሮጀክት ውስጥ የኢዛቤል ባለቤት ዶኮሎ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን
ዶላር ራሱን ሸልሟል። ከዚህ ስምምነት የአንጎላ ሕዝብ የሚያገኘው ጥቅም ምንም ሲሆን በአንጻሩ ለኩባንያው መሥሪያ ተብሎ ከግል ባንክ ለተበደሩት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይከፍላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአንጎላ መንግሥት አልማዝ በዝቅተኛ ዋጋ መሽጡን ቢያምንም ምንጮች እንደሚሉት ግን እስከ
1 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል። ከዚህ ጀርባ ማን ሊኖር ይችላል ሲባል ደግሞ የብዙዎቹ ግምት ኢዛቤል ደ ሳንቶስና ባለቤቷ መሆናቸውን አብዛኛው የአገሬው ሰው ይረዳዋል። ከመሬት ጋር በተያያዘ ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ መሬት ላይም ሁነኛ ተሳታፊ ናቸው። መረጃው እንደሚያሳየው ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ በ2017 በዝቅተኛ ዋጋ
መሬት እንድትገዛ መንግሥት አመቻችቶላታል። ይህንን በመዲናዋ ሉዋንዳ የባህር ዳርቻ የሚገኘውን ጋሻ መሬት የገዛችውም በአባቷ ረጅም እጅ በመታገዝ ነበር። ኮንትራቱ የሚለው መሬቱ 96 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ነው። ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ ያወጣችው ግን 5% ብቻ ነው። ምስኪን ቦታው ላይ የነበሩ አንጎላዊያን
ግን ይዞታቸው ለወይዘሮ ዶ ሳንቶስ በመሰጠቱ ከነበሩበት ዋና ከተማዋ ሉዋንዳ 50 ኪሎ ሜተር ርቀው ተጥለዋል። ከመሬት ጋር በተያያዘ በሌላ የኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ፕሮጀክት ከ500 በላይ ቤተሰብ በእርሷ ምክንያት ተፈናቅሏል። * ኢትዮጵያን ጨምሮ ኢንተርኔት በመዝጋት 'የከሰሩ' ሃገራት
ከቴሌኮም ዘርፍ ጋር በተያያዘ ቢሊየነሯ ከቴሌኮም ዘርፍም አንጎላ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ አግበስብሳለች። በአገሪቱ ከፍተኛው የሞባይል ስልክ አቅራቢ ኩባንያ ውስጥ 25 በመቶ ድርሻ አላት። ዩኒቴል የተባለው ይህ ኩባንያ በቀቅርቡ ለኢዛቤል 1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ የሰጣት ሲሆን ቀሪ ኃብቷም ሌላ 1
ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሏል። ይሁንና ሴትዮዋ ከዘርፉ ገንዘብ የምታገኝበት ይህ ብቸኛ መንገድ አይደልም ተብሏል።