
ትግራይ፡ ጦርነቱን ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሽተዋል
Play all audios:

ትግራይ፡ ጦርነቱን ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሽተዋል11 ህዳር 2020 በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የሚደረገውን ጦርነት ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን መሸሻቸውን የሱዳን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት እስከ 200 ሺህ ኢትዮጵያውን ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የትግራይ ልዩ ኃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ካሉ በኋላ የአገር መከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ ማዘዛቸው ይታወሳል።
ሮይተርስ የዜና ወኪል በዘገባው ወደ ሱዳን ድንበር የተሻገሩት ስደተኞች ሲቪል ወይም ወታደራዊ ይሁኑ ያለው ነገር የለም።
የስደተኞቹ ቁጥር ትናንት ማክሰኞ 6ሺህ መድረሱን የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ገልጾ ቁጥሩ ከዚህም ሊለቅ እንደሚችል ስጋቱን አስቀምጧል።
Skip ብዙ የተነበቡ and continue readingብዙ የተነበቡቡና መጠጣት ለጤና ጠቃሚ ነው ጎጂ? በምን ያህል መጠን?የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ"ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድገት ሳይሆን 'ሚራክል' ነው ያለው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይሦስት ልጆቹን
በመግደል የተከሰሰው አሜሪካዊ በፖሊስ እየተፈለገ ነው End of ብዙ የተነበቡ
ሮይተርስ የአገሬውን የዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘገበው 6ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ሱዳን የዘለቁት ሉቅዲ፣ ቁዳይማህ እና ሐምዳይት በተባሉ የሱዳን ድንበር አካባቢዎች በኩል ነው። ሌሎች በርካታ ስደተኞችም በአትባራ ወንዝ ዳርቻ ወደ ሱዳን ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
ለአንድ ሳምንት በዘለቀው ጦርነት የደረሰው ጉዳት በጨረፍታ ከጦርነቱ ጋር ተያየዞ እየተሰራጩ ያሉ ሐሰተኛ ምሥሎችና መረጃዎች ሮይተርስ የሱዳን ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ከቀናት በፊት እንደዘገበው ደግሞ የጦርነቱን ማገርሸት ተከትሎ የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በከፊል እንደዘጋ
ጽፎ ነበር።
የሱዳን ዜና አገልግሎት እንደሚለው በምሥራቅ ሱዳን አል ቃዳሪፍ ክልል የሚገኘው አስተዳደር ከአማራና ትግራይ የሚያገናኙትን አዋሳኝ ድንበሮችን ላልተወሰነ ጊዜ ዘግቷል።
የዜና አገልግሎቱ ዘገባ እንዳተተው በሱዳን በኩል ሁለቱን የኢትዮጵያ ክልሎች በሚያዋስኑ ግዛቶች አሁን ምርት የመሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ የጦርነቱ ዳፋ የስደተኛ ጎርፍ አስከትሎ ገበሬዎችና ማሳቸው ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል።
በጎረቤት አገር የሚደረገው ጦርነት ያሳሰበው የሱዳን መንግሥት የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ ልዩ ስብሰባ መቀመጡንና በጉዳዩ ዙርያ መምከሩም ተዘግቧል።
የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ያሲን ኢብራሂም ይህን ስብሰባ ተከትሎ እንዳሉት በጎረቤት አገር ኢትዮያ ያለውን ሁኔታ በአንክሮ እየተከታተሉት እንደሆነና ሁለቱም ተዋጊ ወገኖች ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለሱ ማሳሰባቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ እንደገለጠው አብደላ ሐምዱክ ለኢትዮጵያ አቻቸው ዐቢይ አሕመድ አራት ጊዜ ያህል እንደደወሉላቸውና ከህወሓት ጋር ለድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ እንደወተወቷቸው ይኸው ጋዜጣ ዘግቧል።
የፎቶው ባለመብት, Fana
አቶ ገዱ በሱዳን ይህ በአንዲህ እንዳለ የኢፊዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው የተመደቡት አቶ ገዱ አንዳጋቸው ሱዳን ገብተዋል ሲሉ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
አቶ ገዱ ወደ ካርቱም ያቀኑት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ለሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ለማድረስ ነው።
አቶ ገዱ ከሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ መነጋገራቸውም ተዘግቧል።